ኢትዮጵያ እና ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ እና ማስታወቂያ ሁለታቸው አብርው ለመሄድ የተቸገሩ ይመስላል ኢትዬጵያ የራሶ የሆነ ባህል፣ቋንቋ፣አለባበስ ስርዓት፣የአመጋገብና ሌሎችንም ስርዓት የምትከተል ሀገር ናት፡፡ ታድያ በኢትዮጵያ የሚሰሩ ማስታወቂዎች የኢትዮጵያንን ሁለተና ገፅታ የሚያሳይ አይደለም ይልቁንም ከዚያም አልፎ በማስታወቂያ አስተዋውቆ ስለሚሸጠው ምርትና ጠቀሜታ ታሳቢ ተደርገው የሚሰሩ ማስታወቂያወች ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ ምርትን ለመሸጥ መሰርት ያደርጉ ማስታወቂያወች ከዚህ በስተጀርባ ያለውንና የሚያመጠውን ጉዳት ታሳቢ አለመሆናቸው ለኢትዮጵያ እጅግ አሳሳቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ማስታወቂያዎች ከኢትዮጵያ አልፈው በመሄድ ከውጭ ሀገር ከሚሰሩ ማስታወቂያዎች የተኮርጁ (የተቀዱ) ናቸው፡፡
ታድያ እነዚህ ማስታወቂያዎች ከመኮርጃቸው በፊት ታሳቢ መደርግ ያለባቸው ነገሮች ታሳቢ አለመሆናቸው ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከውጭ ተኮርጀው ወደ ኢትዮጵያ ማስታወቂያዎች መተው መሰራታቸው ለኢትዮጵያ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዘነ ነው፡፡ ለምን ካልን ደግሞ የውጭ ሀገር ማስታወቂዎች የራሳቸው የሆነ ባህልና ስርዓትን መሰርት አድረገው የተሰሩ ናቸው ከዚህም በተጨማሪ በሀገሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ተስማምተውና ፈቅደው የሚሰሩ ማስታወቂያዎች ናቸው፡፡ ታድያ የውጭ ሀገሮችን ማስታወቂያ ተኮርጀው ወደ ኢትዮጵያ ማስታወቂያ መጥተው መሰራታቸው የኢትዮጵያዊያኑን ባህልንና ስርአትን እንዲሁም ለሰዎች ዕይታ ያልተመቸና ተፃራሪ በመሆን ይገኛል፡፡
ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ የሚሰሩ ማስታወቂያዎች የኢትዮጵያኑን ባህልንና ስርዓትን አለማፀባርቃቸውና እንዲሁም የሰዎችን ስብዕናን አለመከተሉ በማስታወቂያው ዘርፍ በዘልማድ የሚሰሩ መሆኑንና እንዲሁም በሚሰሩት ማስታወቂዎች ላይ ትኩርት ባለመኖሩ እና ማስታወቂያዎች ተመርምርው አለመሰራታቸው እንዲሁም በሙያው ብቁ አለመሆኑንን ያሳያል፡፡
በመሆኑም በኢትዮጵያ የሚሰሩ ማስታወቂያዎች ሁሉንም ያማከለና ሰዎች አምነውበትና ፈቅደው መሰራት ይኖርባቸዋል ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያኑን የሙያ ፈጠራን መከተል ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም በሙያው የሰለጠነ የሰው ሀይል እንደሚያስፈልግ ያመለከታል፡፡
በመሆኑም በኢትዮጵያ የሚሰሩ ማስታወቂያዎች ሁሉንም ያማከለና ሰዎች አምነውበትና ፈቅደው መሰራት ይኖርባቸዋል ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያኑን የሙያ ፈጠራን መከተል ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም በሙያው የሰለጠነ የሰው ሀይል እንደሚያስፈልግ ያመለከታል፡፡
ከዚህም በመቀጠል ስራው ያማርና የሀገሪቱን ስርዓት የተከተለ እንዲሆን በማሰታወቂያ ሙያ የሰለጠኑ ሰዎች በኢትዮጵያ የሚሰሩ ማስታወቂያዎችን መሰራት ይኖርባቸዋል፡፡ ምክንያቱ ደግም በማስታወቂያ ሙያ የሰለጠነ ሰው ማስታወቂያውን መስራቱ ያለውን ስህተት ለይቶ እንዲሰራ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ የሚሰሩ ማስታወቂዎች በአጠቃላይ ያለባቸውን ችግሮች ለመቀርፍ በማስታወቂያ ሙያ የሰለጠነ ሰው ያስፈልጋል ብየ አምናለሁ፡፡