Wednesday 17 May 2017

                        አወዛጋቢው ማስታወቂያ

የኛ ምርት ያልሆኑ ተመሳሳይ ምርቶችን የሚያመርቱ ግለሰቦች እንዳሉ ደርሰንባቸዋል ? ጉዳዩን በህግ የያዝነው ቢሆንም ..........

እውነት ነው አንዳንድ ማስታወቂያወች እንደዚህ አይነት ዘዴን በመጠቀም ያስተዋውቃሉ ታድያ ለምን በዚህ አይነት ዘዴ ያስተዋውቃሉ ካልን ደግሞ ይህን ማስታወቂያ የሚያዳምጡ ሰዎች አትኩርት ሰጥተው እንዲያዳምጡ ሊሆን ይችላል፡፡ በርግጥ የዚህን ማስታወቂያ በደንብ መርምርንና አገናዝበን ካሰብነው የእኛ ምርት ከሌሎች ምርቶች የተለየና ጠንካራ ነው የሚልም መልዕክት ያለው ማስታወቂያ ነው ፡፡

ለምሳሌም ፀሀይ ቆርቆሮ ማስታወቂያ በሚያስተዋውቅበት ጊዜም የዚህን ዓይነት ማስታወቂያ ተጠቅሞዓል፡፡
(ልብ ይበሉ ፀሀይ ቆረቆሮን ህገ ወጦች አስመስለው እየሰሩት እንደሆነ ደረሰንበታል በህግ እንዲጠየቁም አድርገናል ወደፊትም በተመሳሳይ ህገ ወጥ ስራ የሚሰሩትን በመከታተል በህግ ተጠያቂ ማድርጋችን እንቀጥልበታለን)
    ታድያ ይህ ማስታወቂያ በውስጡ ብዙ መልዕክቶች የያዘ ነው ለምሳሌም ምርቱ ከፍተኛ የሆነ በሰወች ተደማጭነት እንዲያገኝ ያደርገዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰዎች አንድን ማስታወቂያ በሚመለከቱበት ሰዓት ምን አለ ምንስ አለች የሚል ነገር በሚኖርበት ሰዓት ሰዎች በተፈጥሮ አቸው ለተነገርው ነገር ትኩርት እንዲሰጡት ያደርገዋል፡፡

በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ አጭበርባሪ ነው ብየ ብናገር  እውነት ነው ለምን ካላችሁ ደግሞ የዚህ ማስታወቂያ አላማው ምርቱን ማስተዋወቅ ሁኖ ሳል ይህ ማስታወቂያ ግን በተዘዋዋሪ ተዘርፌአለሁ ድርሱልኝ የሚል መልዕክትን እያስተላለፈ ምርቱን መስተዋወቁ ነው ፡፡

በርግጥ ይህ ድርጅት ማስታወቂያ አያስተዋውቅ ማለቴ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንደተበደለ ሰው ተዘርፊያለሁ ድርሱልኝ እርዱኝ እያለ ሰወች ምርቱን እንዲገዙት ማድርጉ ግን የድርጅቱን ታማኝነት ከመቸውም በላይ ሊያጠፋው ይችላል፡፡

ነገር ግን  የማስታወቂያ ዘዴውን መቀየር ይኖርበታል፡፡ ይህ ማስታወቂያ ለመሸጥ ሲል የዚህን አይነት ማስታወቂያ መጠቀሙ እንደ ውሸት ተቆጥሮ ሊያስቀጠው ይችላል፡፡ በመሆኑም ይህ ከመሆኑ በፊት ከዚህ የተሻለን ፈጠራን በመጠቀም ማስተዋወቅ ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን ግዙኝ እርዱኝ የሚሉን መልዕክት የያዙ ሀሳቦችን መጠቀሙ አግባብነት የለውም ፡፡
በመሆኑም የዚህ ማስታወቂያ ዋናው አላማው ሰወች ስለሚያስተዋውቀው ነገር አትኩሮት ሰጥተው እንዲያዳምጡት የማድርጊያ ዘዴ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment