Thursday 11 May 2017

ህንፃ የሴቶች ፋሽን ማስታወቂያ


                                        
                  






   ይህ ማስታወቂያ ከማስታወቂያነቱ ባለፈ የአንዲትን ሀገር የአለባበስ ስረዓትና ባህልን የተላለፈ ነው፡፡ አንድ ሀገር ከሌላው ሀገር የተለየ የአለባበስ ስርዓት አለው፡፡ ታድያ ህንፃ የሴቶች ፋሽን ማስታወቂያ የኢትዮጵያዊያንን የአለባበስ ስርዓትን የሚያዛባ ነው፡፡ ለምን ካልን ደግሞ በዚህ የመሸጫ ሱቅ በውስጡ የኢትዮጵያን ባህል ያማከለ አለመሆኑ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ አልፎ የውጭ ሀገርን የአለባበስ ስርዓት የተከተለ የልብስ ዓይነት ነው፡፡ ሆኖም የአንዱ ሀገር ባህል የሌላኛውን ሀገር ባህልን መሰረት ያደረገ ማስታወቂያ አለመሆኑ ነው፡፡

    ህንፃ የሴቶች ፋሽን ማስታወቂያ ዋናው ችግሩ የአንዲትን ሀገር የአለባበስ ስርዓት አለመከተሉ ነው ታድያ አንዲት ሀገር የራሱን የአለባበስ ባህል ጠብቃ እንድትሄድ ያደርጋታል? ፡፡ ይህ ደግሞ የአንዲትን ሀገር ማንነትና የራሶን የአለባበስ ባህልን ያጠፍባታል ለምሳሌ ብንጠቅስ የሴት ልጅ ሱሪ መልበስና ከጉልበት በላይ የሆኑ ልብሶችን መልበስ በኢትዮጵያዊያን በቀደምት ሰዎች ዘንድ ፈፅም ያልተለመደ ነበር፡፡ ታድያ እንዴት መጣ ካልን ደግሞ እንደ ህንፃ የሴቶች ፋሽን ከውጭ ያሉ ልብሶችን በማምጣት ሰዎች እንዲጠቀሙት ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል ታድያ ይህ በሚሆንበት ሰዓት ሰዎች ይህን ምርት ያለበሰ አራዳ ወይንም ዘመናዊ ሰው አይደለም እያሉ የራሳቸውን ምርት እንዲሸጥላቸው ያደርጋሉ፡፡

   ታድያ ህንፃ የሴቶች ፋሽን በውስጡ ያሉ ልብሶች ለመሸጥ በዘመናዊነት ማምጣቱ ጥሩ መስሎ ቢታይም ከመሸጥ በስተጀርባ ያለውን የአንዲትን ሀገር የአለባበስ ስርዓት የተከተለ መሆኑን ይኖርበታል ፡፡ በርግጥ ማስታወቂያ የአንድን ምርት ለማስተዋወቅና ምርቱ እንዲሸጥለት ማድርግ ቢችልም ጥቅም እንዳለው ሁሉ ጉዳቱንም ለይቶና አውቆ ማስተዋወቅ ይኖርበታ፡፡

   ህንፃ የሴቶች ፋሽን መከተል ያለበት ነገር ቢኖር እኔ የምሸጥላቸው ሰወች ምን አይነት ባህል እና ምንስ ዓይነት የአለባበስ ስርዓት የሚከተሉ ናቸው ብሎ ለሚሸጥላቸው ሰዎች ከመሸጡ በፊት ጥናትና እውቅናው መኖር ይኖርበታል፡፡ ታድያ ይህ ካልሆነ ደግሞ ሰዎች የራሳቸውን ባህል በመተው ወደ ሌላኛው ሀገር የአለባበስ ስርዓት ይሳባሉ ይህ ደግሞ የሚያስከትለው ችግር ትንሽ መስሎ የሚታይ ቢመስልም ችግሩ ግን ብዙነው ፡፡ ምክንያቱ ደግም አንድ ሀገር ካለው የአለባበስ ስርዓት እንዲወጣና ባህሉ እንዲጠፍ ያደርጋል፡፡ ታድያ ህንፃ የሴቶች ፋሽን የሰወችን የአለባበስ ባህልና ስርዓት መጠበቅ ይኖርበታል፡

1 comment:

  1. Best Merkur Safety Razors | Merkur | Connaught
    Merkur Safety Razors Merkur 제왕카지노 is best known for their stylish, close-to-perfect shaving 메리트 카지노 equipment, but their balance worrione is very high in number and

    ReplyDelete