የባዝሊን ሎሽን ማስታወቂያ
ይህ የባዝሊን ሎሽን ሲሆን ማስታወቂያውም
ባዝሊን ሎሽን እንዴት አድርጎ ገላን እንደሚያለሰልስ የሚገልፅ ነው ነገር ግን ይህ ማስታወቂያ ስለ ሴት ልጅ ክብር የሚነካና ስድ የሆነ ማስታወቂያ ነው ምክንያቱም እሴትን ልጅ እርቃንዋን ወይንም እብድ
መሆኖን ይገልፃል ይህ ማስታወቂያ በተለይ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ አፀያፊና
ከሰው ልጅ ስብዕና ጋር የሚፃረር ነው፡፡
ምንም እንኮን ማስታወቂያ በሚሰራበት ጊዜ
ፈጠራንና የሰወችን ቀልብ መሳብ ቢኖርበትም ይህ የባዝሊን ሎሽን ማስታወቂያ ግን በተለይ የኢትዮጵያዊያንን ባህል የሚፃረር ነው ፡፡
በመሆኑም ይህ የባዝሊን ሎሽን በሚያስተዋውቅበት ጊዜ አነማን ናቸው የኔ ተጠቃሚ ፣ ምንስ አይነት ባህል ያለው ማህበርሰብ ነው ፣
ከሚያስተዋውቀው ማሂበርሰብ ጋር አብሮ የሚሂደው ማስታወቂያ የየትኛው ሀገር ባህል ነው በማለት ማስታወቂያው መሰራት ይኖርበታል ፡፡
ነገር ግን ይህ የባዝሊን ሎሽን ማስታወቂያ
እራሱን በዚህ አካሄድ ከማስተዋወቁ በፊት ግንዛቤና ምርምር ማድርግ ነበርበት ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የሌላ ሰው ስብዕናን ስለነካ የሌላ
ሰው ክብርን መንካቱ ደግሞ በሰዎች ዘንድ ቁጣና እንዲሁም ስለምርቱ ያላቸው ፍላጎት እንዲቀንስ ያደርጋል ታድያ ይህ ከመሆኑ በፊት
ስለ ምርቱ መሸጥ ብቻ ሰይሆን ስለ ሰዎች ማሰብ ይኖርበታል ፡፡
ታድያ ይህ የባዝሊን ሎሽን ማስታወቂያ ምንም
እንኳን እራሱን ማስተዋወቅ ቢኖርበትም የአንዲት እሴትን ገላ ወይንም እርቃኑዋን ሁና ባዝሊን በመቀባት ሳይሆን የሴትን ክብር በማይነካ
መልኩ መሆኑ ይኖርበታል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰወችን በሚገባቸው መልኩና ቀለል ያለ አገላለፅን በመጠቀም ወይንም የተጠቃሚውን ባህልን
መሰርት ያደርገ የሎሽን አጠቃቀም ስርዓትን አግባብነት ባለው ሁኔታ መሆን ይኖርበታል፡፡
No comments:
Post a Comment